FidelTypingን እንወቅ
FidelTyping የኢትዮጵያ ፊደላትን ኮምፑተር ላይ መጻፍ ቀላል መሆኑን እንዲያሳይ እንዲሁም በቀላሉ መለማመድ እንዲያስችል በቅጡ ታስቦበት የተዘጋጀን ድህረ-ገጽ ነው። ይህን ድህረ-ገጽ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲጠቀመው በይፋ ማስተዋወቅ በመቻላችን እጅግ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል።
Fideltyping 9 የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን የፊደል ገበታ (አማርኛ፣ትግሪኛ፣አዊኛ፣ሰባትቤት፣ስልጤኛ፣ሐረሪኛ፣ቤንችኛ፣ሙርሲኛ እና ግዕዝን) እንዲሁም እንግሊዘኛን በመጠቀም ኮምፑተር ላይ አተያየብ በማይሰለች መልኩ ያስለምዳል። በተጨማሪም የኢትይትጵያ ቋንቋዎች ፊደላት በ unicode ስርዓት ውስጥ እንዲመዘገቡ መደረጉ እጅግ የሚያስመሰግን የብዙዎች ጥረት እና ስኬት ቢሆንም አንድ ወጥ የሆነ መተየቢያ ስርዓት (keyboard layout) ያለመኖሩን ከግንዛቤ በማስገባት ቢያንስ ሦስት ዋና ዋና እና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይጠቀምባቸዋል ተብለው የታስቡትን ማለትም ለ Windows OS ተጠቃሚዎች (Windows IME), ለ Linux OS ተጠቃሚዎች (Linux IBUS), እና በሁሉም OS መስራት የሚችለውን (Keyman) እንደየፍላጎት በመምረጥ መለማመድ እንዲቻል በFideltyping ተካተዋል።
ሦስት የትየባ ክህሎት ደረጃዎች
FidelTyping ሦስት የክህሎት ደረጃዎችን ለይቶ እንደያሉበት የክህሎት ደረጃ ተገቢውን መሰልጠኛ ያቀርባል።
- ፊደል ተራ (ጀማሪ)፦ ፊደል በፊደል ይማሩ። እያንዳንዱን የኢትዮጵያ ፊደል ለመተየብ የሚያስፈልጉ ቁልፎችን እጅግ ቀላል በሆነ ዘዴ እያመለከተ የሚያለማምድ እና መሠረት የሚያስይዝ ነው።
- ቃላት (መካከለኛ)፦ ቃላትንና ሐረጎችን በመተየብ የጣቶችን ቅልጥፍና እና ፍጥነት የሚያሳድጉበት። ቁልፎቹን በዓይን ሳያዩ በ 100% ትክክለኛነት መተየብ ወደሚችሉበት ደረጃ የሚሸጋገሩበት ነው።
- ቅልጥፍና (ሊቅ)፦ ከእውነተኛ ይዘቶች (ዜናዎች፣ ሕጋዊ ሰነዶች እና ምርምሮች) የተወሰዱ አንቀጾችን በመተየብ ብቃትን የሚያረጋግጡበት። የራስዎንም ጽሁፍ አስገብተው መለማመድ ይችላሉ።
ዋና ዋና ገጽታዎች
- ጨዋታዊ አቀራረብ፦ በFidelTyping መለማመድ በፍፁም አይሰለችም። የኮምፑተር ጨዋታ እንደመጫዎት አይነት ስሜት የሚሰጥ በመሆኑ አእምሮ ላይ ምንም ጫና ሳታሳድር እያዝናና ያስለምዳል።
- ሁሉን አቀፍነት፦ Keyman፣ Windows IME፣ እና Linux IBUS መተየቢያ ስርዓቶችን ማካተቱ እንዲሁም ደግሞ እንግሊዘኛን ጨምሮ ከ 9 በላይ ቋንቋዎችን ማቀፉ ሁሉን አቀፍ ያደርገዋል።
- ውጤት ተኮር፦ የተለማመዱት ምን ያህል ለውጥ አንዳመጣ ለማወቅ መገመት የለበዎትም። Fideltyping ከቅጽበታዊ ግብረ-መልስ ጀምሮ በቀኑ፣ በሳምንት እና በወራት ያዳበሩትን ለውጥ እየተነተነ ለመረዳት በሚቀል መንገድ ያቀርባል። በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያየ ዘርፍ አማካኝ የትየባ ፍጥነት እያጣቀሰ እራስዎን እያነጻጸሩ እንዲያሻሽሉ ያበረታታል። ፍጥነዎና ትክክለኛነትዎ እየተሻሻለ ካሉበት ደረጃ ወደ ቀጣዩ እርከን ሲደርሱ አበረታች ሽልማትም ይቸራል።
- ለትየባ አስተማሪዎች፦ FidelTyping እንደ ተማሪ ሆነው የሚለማመዱበት ብቻ ሳይሆን የአስተማሪ ሚና መርጠው ከተመዘገቡ ተማሪችዎን በቀላሉ መዝግበው የሚከታተሉበት ሰሌዳ ያቀርባል። አስተማሪዎች የክፍሎቻቸውን መለያ ቁጥር ፈጥረው ለተማሪዎቻቸው በማጋራት፣ ተማሪዎች ደግሞ አስተማሪዎች የሚሰጧቸውን መለያ ቁጥር ተጠቅመው ትክክለኛ ክፍላቸውን መቀላቀል እንዲችሉ ያመቻቻል። ስለዚህ ወላጆች የልጆቻቸውን ለወጥ እያዩ እንዲያበረታቱ፣ አስተማሪዎች ደግሞ የተማሪዎቻቸው የትየባ ክህሎት ምን አያህል እያደገ መሆኑን ዕለት በዕለት እየተከታተሉ አስፈላጊውን ምክር እንዲሰጡ ቀላል ሁኔታ ይፈጥራል።
- ያለ ኢንተርኔትም መስራቱ፦ በኮምፑተር ላይ መጫን እንዲቻልና ኢንተርኔት በማይኖርበት ጊዜም እንዲሰራ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ኢንተርኔት በማይኖር ጊዜ የተለማመዱት መረጃ በኮምፑተርዎ ላይ ተቀምጦ ይቆይና ኢንተርኔት ሲያገኝ በራሱ ወደ አካውንትዎ እንዲቀመጥ በማድረግ በሌላ ኮምፑተር ወደ Fideltyping አካውንት በሚገቡ ጊዜ በመጀመሪያው ኮምፑተር ላይ የተለማመዱቱን መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችልበት አሰራር ተካቶለታል።
ማስታወሻ፦ FidelTypingን እንደ Progressive Web App (PWA) በመጫን ያለ ኢንተርኔት መለማመድ ይችላሉ!
- የብቃት ምስክር ወረቀት:- በFideltyping የምዘና ፈተናዎችን ሲወስዱ የምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ለስራ ቅጥር እንደ ተጨማሪ ክህሎት ማስረጃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የሙያ እድገት፦ በትየባ ብቃትዎ የምስክር ወረቀት ያግኙ፤ እንዲሁም በተረጋገጠ የብቃት ማስረጃ የሥራ ቅጥር ዕድልዎን ያስፉ።
-
አማራጭ የገጽ ቀለማት:- ተጠቃሚው እንደየግል የቀለም ጣዕም እና የብርሃን ሁኔታ ቀለማትን እንዲመርጥ አምራጭ የገጽ ቀለማት ተካተዋል።
-
ግላዊነትን ያከብራል:- ሙሉ የFideltyping ጥቅሞችን ለማግኘት አካውንት መክፈት የሚያስፈልግ ሲሆን፣ አካውንት ለመክፈት ደግሞ በጣም ዝቅተኛ መረጃ ብቻ እንዲጠቀም በማሰብ ስምና ትክክለኛ ኢሜል ብቻ ይጠይቃል። ተጠቃሚው የተመዘገበበት ስም፣ ኢሜል እና የልምምድ መረጃዎች ለማንም የማይጋሩ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። በሚቀርበው የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ተጠቃሚው እንዲታይ ካልፈቀደ በስተቀር ሙሉ ስም እንዳይታይ ተደርጓል።
ዛሬውኑ ይጀምሩ
ፈጣን እና ትክክለኛ የመተየብ ጉዞ ድህረ-ገጹን ከመጎብኘት ይጀምራል። የዲጂታል ዓለም እየሰፋ ነው፤ ቋንቋዎቻችንም በዚህ ረገድ ከፍተኛ ተዋናይ መሆን ይገባቸዋል። የዚህ ጉዞ ማኅበረሰባችንን ይቀላቀሉ እና በጊዜና በቦታ ሳይወሰኑ መተየብ ይለማመዱ። በውጤቱም ከግለሰብ እርጋካታ ቀጥሎ በየቢሮዎች የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍና መጨመር፣ ዲጂታል አገራዊ ዕቀቅት ማደግ፣ የዕውቀት ሽግግር መላቅና በጥቅሉ ምርታማት እንደሚጨምር እናምናለን።
👉 FidelTypingን ይጎብኙ: fideltyping.com
ለዚህ ስራ መሳካት ቀድመው መሰረት የጣሉ ሰዎችን ማመስገን ተገቢ ነውና ከዚህ ስር ይመልከቱ። በዚህ ዘርፍ የበለጠ መስራት ለምትፈልጉም የዕውቀት ምንጭ ይሆኗችኋል።
FidelTyping — በቅልጥፍና ይተይቡ።
Introducing FidelTyping
FidelTyping is a thoughtfully designed website created to show how easy it is to write Ethiopian scripts on a computer and to provide a seamless practice environment. We are extremely delighted to officially introduce this platform for all users.
FidelTyping facilitates learning the keyboard layout for 9 Ethiopian languages (Amharic, Tigrinya, Awi, Sebat Bet, Silt’e, Harari, Bench, Mursi, and Ge’ez) as well as English in an engaging way. Additionally, while the inclusion of Ethiopian languages in the Unicode system is a commendable achievement of many, the lack of a uniform keyboard layout remains a challenge. To address this, FidelTyping incorporates the three most common typing systems—Windows IME, Linux IBUS, and Keyman—allowing users to practice according to their preference.
Three Levels of Typing Mastery
FidelTyping offers three skill levels to provide appropriate training based on your current proficiency.
- Fidel (Beginner): Learn character by character. This stage builds a solid foundation by indicating the keys required for each Ethiopian character using an intuitive method.
- Words (Intermediate): Increase finger agility and speed by typing words and phrases. This level helps you transition to typing with 100% accuracy without looking at the keyboard.
- Fluency (Expert): Verify your skills by typing paragraphs taken from real-world content (news, legal documents, and research). You can also input and practice with your own text.
Key Features
- Gamified Approach: Practicing on FidelTyping is never boring. It feels like playing a computer game, allowing you to learn and relax without any mental pressure.
- Inclusivity: By supporting Keyman, Windows IME, and Linux IBUS, and covering over 9 languages including English, it is truly inclusive.
- Result-Oriented: You don’t have to guess your progress. FidelTyping provides everything from instant feedback to detailed analytics of your progress over days, weeks, and months. It encourages improvement by comparing your performance with global averages in various sectors. You will also earn encouraging awards as your speed and accuracy improve.
- For Educators: FidelTyping is not just for learners; it offers a dashboard for those who register as teachers to easily manage and monitor their students. Teachers can share classroom IDs, and students can join their respective classes. This allows parents to encourage their children’s progress and teachers to provide daily guidance based on student growth.
- Offline Capability: Designed to be installed on your computer and work without an internet connection. Your practice data is saved locally and automatically syncs to your account once you go online, ensuring your progress is accessible from any computer.
Tip: You can install FidelTyping as a Progressive Web App (PWA) to practice even without an internet connection!
- Certification: FidelTyping generates certificates when you complete assessment tests, which can be used as proof of skill for job applications.
Professional Growth: Get certified for your typing skills and boost your job applications with verifiable proof of proficiency.
- Customizable Themes: Users can choose from various page color options to suit their personal taste and lighting conditions.
- Privacy-Focused: To enjoy the full benefits of FidelTyping, you only need to provide minimal information (name and a valid email) to create an account. Your registration details and practice data are kept secure and never shared. On leaderboards, user name masked unless the user chooses to be visible.
Start Today
Your journey toward fast and accurate typing begins by visiting the website. The digital world is expanding, and our languages must play a major role in it. Join our community and practice typing anytime, anywhere. We believe this will lead to personal satisfaction, improved service quality in offices, national digital growth, and increased productivity.
👉 Visit FidelTyping: fideltyping.com
We would like to acknowledge those who laid the foundation for this work. They serve as a great source of knowledge for anyone wishing to explore this field further.
FidelTyping — Type with Efficiency.